በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንና የዓለም አቀፍ የጸረ ሽብር ዘመቻ አዲስ ገጽታ


ሪቻርድ ሰተንግል (Richard Stengel)፡ "አንድ ብቸኛ መንገድ የለም። ISIL ወጣቶችን እየፈተረከ የሚወስድባቸው በጅምላ የሚሰሩ የማኅበረሰብ መገናኛዎች አይደሉም ዋነኞቹ መንገዶች። በዚያ አንድ ሰው ላይ የተነጣጠሩ መልዕክቶች፤ የስልክ ግንኙነቶችና የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንን የተጠቀሙ ዘዴዎች ናቸው መንገዶች። የISIL’ን የዩቱብ ቪዲዮዎች በመመልከት ብቻ ጽንፈኝነትን የሚላበስና የራሱ የሚያደርግ ሰው የለም።”

የተለያዩ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙኃንን (Social Media) በመጠቀም ከዓለም ዙሪያ ታዳጊ ወጣቶችን ዓይነተኛ መመልመያ መሳሪያው ያደረገውን ዓለም አቀፍ አሸባሪ ኃይል ISIS’ን አጥፊ፥ ጽንፈኛ ፕሮፖጋዳ ለማምከን እነኚሁኑ የመገናኛ ዘዴዎች ጭምር ለጥቅም ማዋል አዲሱ የፍልሚያ ጎራ ከሆነ ውሎ አደረ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዓለም አቀፍ ሽብርተንነትን ለመዋጋት ተግባር ላይ ያዋለው ይህ አዲስ ውጥን በአሁኑ ሰዓት በኒው ዮርክ በመካሄድ ላይ ካለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ትይዩ በሚደረጉ የተናጠል ውይይቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

ለመሆኑ እነኚህ ጥረቶች የሚፈለገውን ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የቱን ያህል የተሳካላቸው ናቸው? በምንስ ይመዘናሉ?

የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሪቻርድ ሰተንግል (Richard Stengel) ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ግጭት ቀስቃሽ” ያሉት ጽንፈኝነት በአመዛኙ ዓለም አቀፋዊ ይዘት እየተላበሰ እንደመምጣቱ ሁሉን አቀፍ ምላሽ የሚሻ አሳሳቢ ችግር ነው፤ ይሉታል።

ሙሉዉን ዝርዝር አሉላ ከበደ ያቀናበረውን የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንና የዓለም አቀፍ የጸረ ሽብር ዘመቻ አዲስ ገጽታ 5'07"
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:06 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG