በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አባቴ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ተልዕኮ ኢትዮጵያን ማገልገል ነበር” ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት


የሪቻርድ ፓንክረስት - የቀብር ሥነ ስርዓት
የሪቻርድ ፓንክረስት - የቀብር ሥነ ስርዓት

የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪና ወዳጁ የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በመንበረ ፀባዎት ቅድስ ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሰኞ ሊፈፀም የነበረው የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ ስርዓት ወደ ዛሬ ማክሰኞ የተላለፈው ከቤተሰብ በቀረበ ጥያቄ እንጂ ሌላ በምንም ምክንያት አለመሆኑን የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪና ወዳጅ የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በመንበረ ፀባዎት ቅድስ ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡

ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት የሪቻርድ ፓንክረስት - የቀብር ሥነ ስርዓት
ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት የሪቻርድ ፓንክረስት - የቀብር ሥነ ስርዓት

“አባቴ ከእግዜብሄር የተሰጠው ተልዕኮ ኢትዮጵያን ማገልገል ነበር” ብለዋል፡፡ በሥነ ስርዓቱ ላይ የተናገሩት ልጃቸው ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሪቻርድ ፓንክረስት ተሸኙ “አገሬ” በሚሏት “ልጄ” በምትላቸው ምድር የመጨረሻ ስንብታቸው ሆነ፡፡

አስከሬናቸውም የጣሊያንን ወረራ ከኢትዮጵያ ጋር ሆነው ከታገሉት እናታቸው ሲልቪያ ፓንክረስት ጎን አረፈ - በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሰኞ ሊፈፀም የነበረው የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ ስርዓት ወደ ዛሬ ማክሰኞ የተላለፈው ከቤተሰብ በቀረበ ጥያቄ እንጂ ሌላ በምንም ምክንያት አለመሆኑን የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የሪቻርድ ፓንክረስት - የቀብር ሥነ ስርዓት
የሪቻርድ ፓንክረስት - የቀብር ሥነ ስርዓት

ጥያቄው የቀረበው ከውጭ የሚጠበቁ የቤተሰብ አባላት በቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ በማሰብ መሆኑ በሚኒስትር መ/ቤቱ የሕዝብና ዓለምቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል፡፡

ሪቻርድ ፓንክረስትና ቤተሰቦቻቸው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መሆናቸውን የገለፁት አቶ ገዛኸኝ ከቀብር ቦታ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ መስተጓጎል እንዳልነበረ ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“አባቴ ከእግዚአብሄር የተሰጠው ተልዕኮ ኢትዮጵያን ማገልገል ነበር” ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:22 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG