በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኅዳሴ ግድብ እና የዓለምአቀፉ ቡድን ሪፖርት


ኅዳሴ ግድብ
ኅዳሴ ግድብአቶ ምኅረት ደበበ - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ
አቶ ምኅረት ደበበ - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ታዋቂ የሆኑ ጋዜጦችና የዜና ወኪሎች ስለናይል ወይም ስለአባይ ወንዝ እና ስለኅዳሴ ግድብ እየፃፉ ነው፡፡

የኒው ዮርኮቹ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብሉምበርግ፣ ዘ ዋል ስትሪት ጁርናል፣ ዘ ናሽናል ከእነዚያ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ዘ ዋል ስትሪት ጁርናል በረቡዕ፣ ጥቅምት 6/2006 ዓ.ም ዕትሙ ባሠፈረው ዘገባው ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በመጭው ሣምንት ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12/2006 ዓ.ም እንደሚሰበሰቡ የኢትዮጵያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምንጭነት ጠቅሶ ፅፏል፡፡
Ethiopia, Sudan, Egypt, Eritrea
Ethiopia, Sudan, Egypt, Eritrea

ይህ ስብሰባ የሚካሄደው በሦስቱ ሃገሮች የተመሠረተው የኤክስፐርቶች ቡድን የቅኝት ሪፖርቱን ካስገባ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

ቡድኑ ሪፖርቱን ለሃገሮቹ ካስገባ ሦስት ወራት እንደተቆጠሩም ጋዜጣው ጠቁሟል፡፡

ከሦስቱም ሃገሮች ኤክስፐርቶች ተውጣጥቶ በኅዳሴ ግድብ ላይ የቅርብ ቅኝት ያደረገው ይህ ቡድን ያደኋቸው ችግሮች ያላቸውን ወይም የስጋት አካባቢዎችን አንስቷል፤ ይመስሉኛል ያላቸውን ሃሣቦችም አስፍሯል፡፡

በዘገባው መሠረት በኅዳሴ ግድብ መሠረትና መዋቅር ላይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ችግሮች ወይም ስህተቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ዓለምአቀፉ የኤክስፐርቶች ቡድን በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በሪፖርቱ አበይት ነጥቦች እና ሌሎችም ጠቅላላ ጉዳዮች ላይ የግድቡ አሠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ምኅረት ደበበ ለቪኦኤ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ኅዳሴ ግድብ
ኅዳሴ ግድብ
XS
SM
MD
LG