በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራዲዮ መጽሔት ወጎች:- የማሕበረሰብ ደህንነት፥ ሥነ ግጥም፥ ታሪክና ኪነ ጥበብ።


Amharic Radio Magazine Program Banner
Amharic Radio Magazine Program Banner

“የይሁዳ ከንፈር” ትሰኛለች፤ የሳምንቷ ምርጥ ግጥም በወጣቷ ገጣሚ ትዕግስት ዓለምነህ ናት።

“የይሁዳ ከንፈር” ትሰኛለች፤ የሳምንቷ ምርጥ ግጥም በወጣቷ ገጣሚ ትዕግስት ዓለምነህ ናት።

“የይሁዳ ከንፈር” - የሳምንቱ ምርጥ ግጥም፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

በርካታ ምዕተ-ዓመታት በምናብ ወደ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ሊያጓጉዘን በሚዳዳው የታሪክ መጽሃፍ በራዲዮ መጽሔት ያወያያል።

በዐጼ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግስት ከ1520-1527 የፖርቹጋል ንጉስ መልዕክተኞች በኢትዮጵያ ያደረጉትን ታሪክ ጉዞ የሚተርከውና በአባ ፍራንሲስኮ አልቫሬጽ ተጽፎ በሎርድ ስታንሌ ኤልደርሌ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመውን መጽሃፍ ከስልሳ ዓመታት በፊት በአቶ ዮና ቦጋለ ነው ወደ አማርኛ የተመለሰው።

መጽሃፉ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በተመረቀበት ወቅት በመጽሃፉ ይዘት፥ በታሪኩ ተጨባጭነትና አንድምታ ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ጥናታዊ ጽሁፎችን ያቀረቡ የማሕበረሰብና የቋንቋ ምሁራን ተወያይተዋል። ራዲዮ መጽሔት አንደኛውን ጋብዘናል።

በዐጼ ልብነ-ድንግል ዘመነ መንግስት ...
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:54 0:00

ለመሆኑ ተርጓሚው አቶ ዮና ቦጋለ ማናቸው?

አቶ ዘካሪያስ ዮና .. የተርጓሚው የአቶ ዮና ቦጋለ ልጅ ናቸው። ለመሆኑ በሺህ ሃምሳዎቹ የተተረጎመው ይህ መጽሃፍ እንደምን እስከዛሬ ሳይታተም ቀረ? አቶ ዘካሪያስ ስለ መጽሃፉም ስለ አባታቸውም ያወጉናል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:13:24 0:00

ባለፈው እሁድ ልክ የዛሬ ሳምንት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የተካሄደ ዝግጅት ነው።

ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የሕጻናትና የአረጋውያን መርጃ ገንዘብ ለማሰባሰብ ታልሞ የተሰናዳውን ዝግጅት “ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው” .. የሚል መጠሪያ ሰጥተውታል።

የዘንድሮዋን ወ/ሪት ኢትዮጵያ USA’ን ጨምሮ የዝግጅቱ አስተባባሪ እና የሜሪ ጆይዋን መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ይወያያሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:22:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG