ዋሽንግተን ዲሲ —
በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ ለተቃውሞ የወጣ ሕዝብ፣ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመበት መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናገሩ። ይህን መረጃ ያረጋገጠው ተቃዋሚው ፓርቲ የመላ-ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ፣ በዳንግላ ከተማ የሚኖሩት የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ ሙሉቀን ዐይናለም ትናንት መታሰራችውንም አክሎ ገልጿል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግን፣ የነበረው ሰልፍ ሳይሆን ሙከራ ነው፣ የተሳታፊዎቹም ቁጥር አነስተኛ ነው ይላል። በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም የተደረጉ የነውጥ ጥሪዎችም አልተሳኩም ብሏል።
እስክንንድር ፍሬው ዘገባ አለው።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።