በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብልፅግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ


አቶ ብናልፍ አንዱአለም
አቶ ብናልፍ አንዱአለም

ትግራይ ክልል ውስጥ ሲካሄድ የቆየው ወታደራዊ ውጊያ መጠናቀቁንና መቆሙን የገዥው ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ገልፀዋል።

የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የዋና ፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በተለይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወታደራዊ ዘመቻው ያበቃ ቢሆንም “በተወሰኑ ቀናት የሚጠናቀቅና በፖሊስ ኃይል እየተካሄደ ነው” ያሉት “ህግ የማስከበር ዘመቻ የሚጠናቀቀው ግን የህወሓት መሪዎች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው” ብለዋል።

እስካሁን ‘ተሸንፈናል’ ያላለው ህወሓት ይልቁንም ‘ሥልታዊ ማፈግፈግ’ ማድረጉን እየገለፀ የሚገኝ ሲሆን አቶ ብናልፍ ግን እንደዚህ ዓይነት አስተያየቶችንና የተራዘመ የሽምቅ ውጊያ ሊኖር ይችላል የሚሉ ግምቶችን አጣጥለዋል።

ህወሓት በሽብርተኝነት እንዲፈረጅ እየቀረቡ ያሉ ጥሪዎች መኖራቸውን የጠቀሱት የፅ/ቤቱ ኃላፊ ገዥው የብልፅግና ፓርቲ ገና ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ አለመድረሱንም አመልክተዋል።

በሌላም በኩል ወደ 30 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በምዕራብ ትግራይ ሲነሳ የቆየው የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ አግባብነት ባለው መንገድ እንዲመለስ የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መወሰኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል።

የፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኅዳር 25 እና 26 ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ትናንት አጠናቅቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የብልፅግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:21 0:00


XS
SM
MD
LG