በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚያንማር የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል


ፖሊስ በወታደራዊ ኃይሉ የተደረገውን የመንግሥት ግልበጣ ለመቃወም አደባባ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ውሃ ሲረጭ
ፖሊስ በወታደራዊ ኃይሉ የተደረገውን የመንግሥት ግልበጣ ለመቃወም አደባባ በወጡ ተቃዋሚዎች ላይ ውሃ ሲረጭ

በቅርቡ የሚያንማርን መንግሥትን ያስወገደው እና ሥልጣኑን የተቆጣጠረው ወታደራዊ ቡድን የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጧል። “በውጥረት እና በብጥብጥ ጊዜያት ኢንተርኔትን ማቋረጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስልት እየሆነ መጥቷል።

በዚህ ሣምንት የሚያንማርን ሥልጣን የተቆጣጠረው ወታደራዊ ኃይል የኢንተርኔት አገልግሎቱን አቋርጧል። በዚህ ደግሞ ዜጎች እርስ በእርሳቸው እንዳይገናኙ እና ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ በቂ መረጃ እንዳይኖራቸው አድርጓቸዋል። በተጨማሪም ጋዜጠኞች ቀውሱን በተመለከተ መረጃ ማጠናቀር እና ያጠናቀሩትን መረጃ ለሕዝብ በማድረስ ላይም እክል ገጥሟቸዋል።

ድንበር ተሻግራ ከምትገኘው ታይላንድ ለበርማ የዜና አገልግሎት የምትሠራው ናይን ናይን የሥራ ባልደረቦቿን ማግኘት እንደተቸገረች ገልፃለች። “ጠዋት ላይ የዕለቱን ዘገባችንን እንዴት እንደምናጠናቅር ስብሰና ነበረን ነገር ግን ሁሉም የሥራ ባልደረቦቻችን የመገናኛ መስመር ተቋርጧል። የሥራ ባልደረቦቼ ከኔትወርክ ውጪ ናቸው። ወታደራዊ ኃይሉ ኢንተርኔት ብቻ ሳይሆን ስልክም አቋርጧል።” ብላለች።

ላለፉት በርካታ ዓመታት በሚያንማር የኢንተርኔት መዘጋት ሁኔታ ተደጋግሞ እየተከሰተ ነው። ለምሳሌ ራሂን እና ቺን ከተማን ብንመለከት የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳልነበራቸው አንዳንድ ጊዜም የተገደበ አገልግሎት እንደነበራቸው እንገነዘባለን። ይህን ሁኔታ እንደ ዩጋንዳ፣ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል፣በቤላሩስ፣ እና ሕንድን ከመሳሰሉ ሃገሮች ጋርም ስናስተያየው ረዘም ላለ ግዜ በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ ተቃውሞ እና ሕዝባዊ አመፅ በሚኖርበት ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት ሲቋረጥ ተስተውሏል።

በካሽሚርም የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል ሕንድ ይህንን ያደረገችው አክራሪነትና የሐሰት ዜናዎችን ለመዋጋት መሆኑን ስትገልፅ ቆይታለች።

የኢንተርኔት መቋረጥ ፣የአገልግሎቱ ቀርፋፋ መሆን እንዲሁም የድረ ገፆች መታገድ መረጃን ለማኅበረሰብ የማድረስን ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንተርኔት መቋረጥ የመረጃ ተደራሽነትን የበለጠ አስቸጋሪ ያደርገዋል ይላል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነት ልዩ ፀሐፊ ኢሪን ካህን ስለዚሁ ሲናገሩ፤

“እንደዚህ ያሉ አካሄዶች የሰዎችን መረጃ የማግኘት መብት ለመቁረጥ የሚያገለግሉ በጣም ደብዛዛ መሳሪያ ናቸው።” ይላሉ።

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሚያንማር ያለው የኢንተርኔት ሁኔታ ተለውጧል ፣ ጋዜጠኞች እና የመብት አራማጆች በበኩላቸው አገልግሎቱን ለማግኘት እየጣሩ መሆኑን ተናግረዋል።

(በቪኦኤ ዘጋቢ ኢሻ ሳሪ የተናቀረ ዘገባ በጽዮን ግርማ ወደ አማርኛ ተመልሷል)

በሚያንማር የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00


XS
SM
MD
LG