No media source currently available
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የልኡካን ቡድናቸውን ይዘው ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ጠብቋቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ባለፈው ሳምንት ኤርትራን ሲጎበኙ ባደረጉላቸው ግብዣ ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከመድፍ ተኩስ እስከ ቤትመንግስት የመቀበያ ምሳ ግብዣ የደመቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።