በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአርባ አንደኛው ፕሬዚዳንት ገድልና ሽኝት

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ቀዳሚት እመቤት ሜላንያ ትረምፕ የተወካዮች ምክር ቤቱ እልፍኝ ተገኝተው ለጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አስከሬን ክብር ሲሰጡ። ሰኞ፤ ኅዳር 25/2011 ዓ.ም.
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ቀዳሚት እመቤት ሜላንያ ትረምፕ የተወካዮች ምክር ቤቱ እልፍኝ ተገኝተው ለጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አስከሬን ክብር ሲሰጡ። ሰኞ፤ ኅዳር 25/2011 ዓ.ም.

ስለፕሬዚዳንት ቡሽ ክብር እየተከናወነ ያለው ሥነ-ሥርዓት በክብር ዘብና በመዘምራን የታጀበም ሲሆን የዛሬና የቀድሞ የአሜሪካና የአውሮፓ መሪዎች ከፍ ያሉ ትውስታዎቻቸውን እየዘከሩላቸው ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አስከሬን ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ በተወካዮች ምክር ቤቱ ዋና እልፍኝ አርፎ ሰዉ እየተሰናበተ ነው።

ስለፕሬዚዳንት ቡሽ ክብር እየተከናወነ ያለው ሥነ-ሥርዓት በክብር ዘብና በመዘምራን የታጀበም ሲሆን የዛሬና የቀድሞ የአሜሪካና የአውሮፓ መሪዎች ከፍ ያሉ ትውስታዎቻቸውን እየዘከሩላቸው ነው።

የዩናይትድ ስቴትስን ባንዲራ የለበሰው የአርባ አንደኛውን ፕሬዚዳንት ጆርጀ ኤች ዳብልዩ ቡሽን አስከሬን የያዘው ሣጥን በጦር ኃይሎች ጥምር የክብር ዘብ ታጅቦ ካፒቶል እልፍኝ እንደደረሰ /ሰኞ፤ ኅዳር 24/2011 ዓ.ም./
የዩናይትድ ስቴትስን ባንዲራ የለበሰው የአርባ አንደኛውን ፕሬዚዳንት ጆርጀ ኤች ዳብልዩ ቡሽን አስከሬን የያዘው ሣጥን በጦር ኃይሎች ጥምር የክብር ዘብ ታጅቦ ካፒቶል እልፍኝ እንደደረሰ /ሰኞ፤ ኅዳር 24/2011 ዓ.ም./

የፕሬዚዳንት ቡሽ አስከሬን ትናንት /ሰኞ/ ተስያት የተወካዮች ምክር ቤቱ ወይም የካፒቶል እልፍኝ እንደደረሰም ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የሚስተር ቡሽን የሕይወት ዘመን የመንግሥትና የሕዝብ አገልግሎት አስበዋል።

የተወካዮች ምክር ቤቱ ተሰናባች አፈ ጉባዔ ፖል ራያንና የሕግ መወሰኛው የአብላጫዎቹ መሪ ሚች ማክኮኔል ጆርጅ ቡሽን ያስታወሱት ከፍ ባለ ክብር ነበር።

የጀርመን መሪ አንጌላ መርከል ስለ ፕሬዚዳንት ቡሽ ሲናገሩ “... የጀርመን ውኅደት አባት ወይም ከአባቶች አንዱ ናቸው ...” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአርባ አንደኛው ፕሬዚዳንት ገድልና ሽኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:39 0:00
የአርባ አንደኛው ፕሬዚዳንት ገድልና ሽኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG