በአፍጋኒስታን ዉስጥ በፈንጂ ሰለወደመዉ የመስክ ሆስፒታልና በዉስጡ ሰለነበሩ 22 ሰዎችና የሌሎች ሁለት ልጆች ሕይወት ግልጽና ሙሉ ምርመራ እንደሚደረግ ፕሬዚደንት ኦባማ ቃል ገብተዋል።
ፕረዚደንት ኦባማ በርግጥኝነት ምን እንደተከሰተ ለማወቅ ጓጉተዋልጆሽ እርነስት የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ
ፕሬዚደንቱ ኩንዱስ ዉስጥ ሰለነበረዉ ሆስፒታል መመታት፣ ትላንት ድንበር የለሽ ሃኪሞች (Doctors Without Borders)የተባለዉን ስብአዊ ድርጅት መሪ በስልክ ይቅርታ ጠይቀዋል። ዜጎቻቸዉ ሰለባ ለሆኑት የአፍጋኒስታን ፕሬዚደንትም የሃዘን መግለጫ ጥሪ አድርገዋል።
የአፍጋኒስታን አክራሪ እስላማዊ ታሊባን ንቅናቄ በሰሜን የምትገኘውን የኩንዱዝ ከተማ ይዘዋል። ናንጋርሃርና ፓክቲካ የሚባሉት ክልልሎች ደግሞ ከአይስስ ጥቃት ደርሶባቸዋል ።
የአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን የቦምብ ድብደባዉ የተካሄደዉ በካቡል መንግስት ጥያቄ እንደሆነ በማመልከት ባለፈዉ ቅዳሜ ለጥቃቱ ሃላፊነትን ወስዷል። የቪኦኤ ዘጋቢ ዘላይትካ ሆክ (Zlatica Hoke) ጥቃቱ እንደ ጦርነት ወንጀል እንደሚቆጠር ለመወሰን፣ ድንበር የሌሽ ሃኪሞች ወገንተኛ ያልሆነ አካል እንዲመረምር መጠየቁን ጠቅሳ ዘገባ ልካለች።
ሰሎሞን አባተ ዝርዝሩን አቀናብሮታል። ይህንን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።