አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት ጋር ተነጋገሩ፡፡ ከዚሁ ከወልቃይት ጋር በተያያዘ በመቀሌ ሰጡት የተባለውን አስተያየት በተመለከተም፣ ምላሽ መስጠታቸውን የኮሚቴው አባል አቶ አታላይ ዛፌ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተደረገው ውይይት ትርጉም የሚኖረው ግን፣ ቀጣይነት ሲኖረውና ውጤት ሲገኝ መሆኑን እኝሁ የኮሚቴ አባል ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎንደር ከተማ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ከተነሱት ዋና ጉዳዮች አንዱ ይሄው የወልቃይት ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ