በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን የሺኣ ሙስሊም መስጊድ ከፍተኛ ፍንዳታ ደረሰ 43 ሰዎች ሞቱ


በሰሜን አፍጋኒስታን ኩንዱዝ ክፍለ ግዛት ብዙ ሰው በተሰበሰበት የሺኣ ሙስሊሞች መስጊድ በተፈጸመ የአጥፍቶ መጥፋት ከፍተኛ የቦምብ ፍንዳታ 43 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 150 የሚሆኑ ቆስለዋል።
በሰሜን አፍጋኒስታን ኩንዱዝ ክፍለ ግዛት ብዙ ሰው በተሰበሰበት የሺኣ ሙስሊሞች መስጊድ በተፈጸመ የአጥፍቶ መጥፋት ከፍተኛ የቦምብ ፍንዳታ 43 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 150 የሚሆኑ ቆስለዋል።

በሰሜን አፍጋኒስታን ኩንዱዝ ክፍለ ግዛት ብዙ ሰው በተሰበሰበት የሺኣ ሙስሊሞች መስጊድ በተፈጸመ የአጥፍቶ መጥፋት ከፍተኛ የቦምብ ፍንዳታ 43 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 150 የሚሆኑን መቁሰላቸው ተነገረ፡፡

አባድ አካባቢ ወይም ኩንዱዝ ተብሎ በሚታወቀው ዋና ከተማ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

የታሊባን መንግሥት ቃል አቀባይ ዛቢሁላ ሙጃሂድ ዝርዝር መግለጫ ባይሰጡም “ጥቃቱ ብዙ ሰዎችን ገድሏል አቁስሏል” ብለዋል፡፡

የታሊባን ኃይሎች በቦታው የነበሩ ሲሆን ምርመራው እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሌላው የታሊባን ባለሥልጣን ባለፈው እሁድ በካቡል የደረሰውን ፍንዳታ ያደረሱት፣ በግዛቱ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎቹ የእስላማዊ መንግሥት አራማጆች መሆናቸውን እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል፡፡ ባላፈው እሁድ በካቡል በትልቁ መስጊድ ላይ በደረሰው ፍንዳታ 8 ሰዎች ሞተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG