በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን የሺኣ ሙስሊም መስጊድ ከፍተኛ ፍንዳታ ደረሰ


በሰሜን አፍጋኒስታን ኩንዱዝ ክፍለ ግዛት ብዙ ሰው በተሰበሰበት የሺኣ ሙስሊሞች መስጊድ በተፈጸመ ከፍተኛ የቦምብ ፍንዳታ ቁጥሩ ያልታወቀ ጉዳት ደርሷል፡፡

አባድ አካባቢ ወይም ኩንዱዝ ተብሎ በሚታወቀው ዋና ከተማ ለደረሰው የቦምብ ጥቃት እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡

የታሊባንመንግሥት ቃል አቀባይ ዛቢሁላ ሙጃሂድ ዝርዝር መግለጫ ባይሰጡም “ጥቃቱ ብዙ ሰዎችን ገድሏል አቁስሏል” ብለዋል፡፡ የታሊባን ኃይሎች በቦታው የነበሩ ሲሆን ምርመራው እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ሌላው የታሊባን ባለሥልጣን ባለፈው እሁድ በካቡል የደረሰውን ፍንዳታ ያደረሱት፣ በግዛቱ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎቹ የእስላማዊ መንግሥት አራማጆች መሆናቸውን እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል፡፡ ባላፈው እሁድ በካቡል በትልቁ መስጊድ ላይ በደረሰው ፍንዳታ 8 ሰዎች ሞተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG