በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በኤርትራው ውሳኔ ላይ የሰጡት አስተያየት


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ሥምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የደረሰበት ድምዳሜ ከኤርትራ ጋር ያለውን ውጥረት እንደሚያረግብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ሥምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የደረሰበት ድምዳሜ ከኤርትራ ጋር ያለውን ውጥረት እንደሚያረግብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ባለፉት ሃያ ዓመታት የነበረውን ሁኔታ “ሞት አልባ ጦርነት” ሲሉ ገልፀውታል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የኤርትራ ባለሥልጣናት "ኤርትራ ከ18 ዓመታት በፊት የተደረገውን የአልጀርስ ውልና ከ16 ዓመታት በፊት የተወሰነውን የድንበር ኮሚስን ውሳኔን ተቀብላ እስካሁን ባለው ጊዜ እንዲተገበር ስትጥርና ስትጠብቅ የቆየች ሀገር ነች" ብለዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ከ18 ዓመታት በኋላ የአልጀርስ ውልንና የድምበር ውሳኔን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀብያለሁ ማለትዋ ኤርትራ ለ18 ዓመታት ያህል ሰትጠይቀውና ስትታገልለት ከቆየው መካከል የተለየ አዲስ ነገር አይደለም ማለታቸውም ታውቋል፡፡

የአልጀርስ ሥምምነትና የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ መተግበር በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ለሚፈጠር አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ቅድመ ሁኔታ ነው ሱሉም ባለሥልጣኖቹ ተናግረዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በኤርትራው ውሳኔ ላይ የሰጡት አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:43 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG