በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓፕዋ ኒው ጊኒ የተራራ ናዳ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎችን ከነሕይወታቸው ቀበረ

በፓፕዋ ኒው ጊኒ አንድ መንደር ውስጥ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ሰዎች ከነሕይወታቸው በተራራ ናዳ እንደተቀበሩ፣ አገሪቱ ለተባበሩት መንግሥታት ቢሮ አስታውቃለች፡፡

መንጋሎ የተሰኘው ተራራ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ ሲናድ፣ ከሥሩ የሚገኘውን ኢንጋ መንደር ሙሉ ለሙሉ አውድሞ ነዋሪዎቿን ከነሕይወታቸው እንደቀበረ፣ ብሔራዊ የአደጋ መከላከያ ቢሮው በመዲናዋ ፖርት ሞርዝቢ ለሚገኘው የተመድ ቢሮ አስታውቋል።

ናዳው፣ በሕንጻዎች እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ውድመት በማድረሱና ዋናው አውራ ጎዳና ሙሉ ለሙሉ በመዘጋቱ፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

ናዳው አሁንም ቀስ በቀስ መንከባለሉን በመቀጠሉ፣ በአደጋ ሠራተኞች እና ከአደጋው መውጣት በሚችሉት ላይ ስጋትን መደቀኑ ተመልክቷል።


XS
SM
MD
LG