በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓፑዋ ኒው ጊኒ ለደረሰው የመሬት መንሸራተት ከፍተኛ ውድመት የርዳታ ጥረቱ ይጨምራል


በፓፑዋ ኒው ጊኒ የደረሰውን እጅግ የከፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ
በፓፑዋ ኒው ጊኒ የደረሰውን እጅግ የከፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ

ከ2 ሺሕ በላይ ሰዎች በቁማቸው የተቀበሩበትን በፓፑዋ ኒው ጊኒ የደረሰውን እጅግ የከፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ጥረቱን ማጠናከሩን የዓለም የህጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ አስታወቀ። እጅግ አደገኛ የመሬት አቀማመጥ እና ርዳታ በፍጥነት ለማጓጓዝ አዳጋች የሆነው ሁኔታ ተደማምረው ካሁን በኋላ በሕይወት የሚተርፉ ሰዎች የመገኘታቸውን ዕድል አናሳ ማድረጋቸው ተመልክቷል።

የዩኒሴፏ ተወካይ አንጀላ ኬርኒ ሲያስረዱም “ከአስከፊው አደጋ የተረፉ ሰዎችን ለመርዳት ከፓፑዋ ኒው ጊኒ ባለሥልጣናት እና የማኅበረሰብ ተቋማት ጋራ በቅርበት እየሠሩ መኾኑን ተናግረዋል። ኬርኒ አክለውም "የአደጋው ሰለባ ከኾኑት መካከል ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወላጆቻቸውን እና መኖሪያቸውን ያጡ፤ እንዲሁም የሚኖሩበት ሁኔታ ከመሰረቱ በመፋለሱ ብርቱ የአእምሮ መናወጥ የገጠማቸው ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊ ሕጻናት መሆናቸው ግልጽ ሆኗል" ሲሉ የአደጋውን ክፋት አስረድተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG