በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓኪስታኑ የመስጊድ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 100 ከፍ አለ


ፓኪስታን ውስጥ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በሰዎች በተሞላ አንድ መስጊድ ውስጥ ትናንት በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 100 መድረሱ ተነገረ፡፡
ፓኪስታን ውስጥ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በሰዎች በተሞላ አንድ መስጊድ ውስጥ ትናንት በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 100 መድረሱ ተነገረ፡፡

ፓኪስታን ውስጥ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በሰዎች በተሞላ አንድ መስጊድ ውስጥ ትናንት በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 100 መድረሱ ተነገረ፡፡ ሌሎች 150 የሚደርሱ ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

ኺበር ፓኽቱንዃ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ማዕከላዊ ፔሻዋር በደረሰው ፍንዳታ፣ ተጎጂ የሆኑ ሰዎችን ከህንጻው ፍርስራሾች ውስጥ የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉም ተነገሯል፡፡ እጅግ አደገኛ እንደነበር የተነገረለት ፍንዳታ የህጻንውን ጣሪያ ማፈራረሱ ተመልክቷል፡፡

ጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል አብዛኞቹ የክፍለ ግዛቲቱ ፖሊሶች መሆናቸው ሲገልጽ፣ አደጋው የደረሰበት መስጊድ፣ በደህንነትና የመንግሥት ባለሥልጣናት የሚዘወትር መሆኑም ተነግሯል።

እስካሁን ለፍንዳታው ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን አለመኖሩ የተገለጸ ሲሆን ፣የፓኪስታኑ ታሊባን ለአሜሪካ ድምጽ የላከውን ጨምሮ ባወጣው መግለጫ በሰኞው ፍንዳታ እጁ እንደሌለበት አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG