በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምያና የሶማሌ ችግር ሶማሊላንድ ላይ ጥቃት አስፈፀመ

በኦሮምያና በሶማሌ ክልሎች ወሰኖች ባሉ ወረዳዎች ውስጥ እየተካሄደ ካለው የጥቃት እርምጃዎችና ግጭቶች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ከተፈጠረው የፀጥታ ቀውስ ጋር ተያይዞ ከሰማሌ ክልል የተፈናቀሉ ከአርባ ሺህ እስከ ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ተፈናቃዮች ምሥራቅ ሃረርጌ መግባታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ ማምሻውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጭናቅሰን ውስጥ ዛሬ በተፈጠረ ግጭት የሦስት ሰው ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚሁ የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ቀውስ ጋር ተያይዞ ጎረቤት ሶማሌላንድ ውስጥ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወት ያጠፋ ጥቃት እየተፈፀመባቸው መሆኑና ከፍተኛ ሥጋት ላይ እንደሚገኙ እየገለፁ ናቸው።

ሃርጌሣ ላይ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተገድለው አንደኛው ላይ ጉዳት እንደደረሰት የሶማሊላንድ የፀጥታ ሚኒስትር ዴኤታ አስታውቀዋል።

ሶማሊያዊያኑ በኢትዮጵያዊያን ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ ጥሪ ያስተላለፉት ሚኒስትር ዴኤታው ሞሐመድ ሙሣ ዴሬ ለኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ጥበቃ እንዲያደርጉ ኃይሎቻቸውን ማዘዛቸውን አመልክተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦሮምያና የሶማሌ ችግር ሶማሊላንድ ላይ ጥቃት አስፈፀመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG