በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ጉጂ የቀንጥቻ ሰው ሰልፍ ወጣ


በኦሮምያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ የቀንጥቻ ቀበሌ ነዋሪዎች ዛሬ ብዙ ሰው የተሣተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ጥያቄዎቻቸው ከአካባቢ ጥበቃ፣ የልማት ተጠቃሚነትና የሥራ ዕድል ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ግዙፉ የታንታላይት ክምችት ያለበት በምሥራቅ ጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የቀንጥቻ ቀበሌ ነዋሪ ዛሬ አደባባይ የወጣው ለብዙ ዓመታት በተለያዩ አጋጣሚዎች ይነሱ የነበሩ የምጣኔ ሃብት፣ የአካባቢ ደኅንነትና የመብት ጥያቄዎችን ይዞ ነው።

የቀንጥቻ የታንታላይት፣ ቦሮማይትና ኳርትዝ ማምረቻ ፋብሪካ ወደ ሦስት አሠርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ሥራ ላይ ቢሆንም ለአካባቢው የሥራ ዕድል እንኳ ካለመክፈቱ በተጨማሪ የአካባቢ ብክለትም እያደረሰ መሆኑን በሰልፉ ላይ የነበሩ አንድ የአካባቢው ነዋሪ አመልክተዋል።

ሌላ ሰልፈኛም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ድንበር ዘለል ጥቃቶች በኦሮሞዎች ላይ እንደሚፈፀሙና የኦሮሞ ልጆች እንደሚገደሉ ጠቁመው “ይህ ሁሉ ለምን ይፈፀምብናል?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የቦሩ ሰባ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ቅጦ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ የሰዉን ጥያቄ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር እየመከሩበት እንደሆነ ተናግረዋል።

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በምሥራቅ ጉጂ የቀንጥቻ ሰው ሰልፍ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG