በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የፕሬስ ቀን


Pakistan World Press Freedom Day
Pakistan World Press Freedom Day

በዛሬው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ዕለት የፕሬስ ነፃነት ድርጅቶች ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉት ጋዜጠኞች ለገጠማቸው ተግዳሮት ትኩረት ሰጥቷል።

በዛሬው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ዕለት የፕሬስ ነፃነት ድርጅቶች ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉት ጋዜጠኞች ለገጠማቸው ተግዳሮት ትኩረት ሰጥቷል።

ጋዜጠኞች ክስ፣ የመንግሥት የኢንፎርመሽን ገደብ፣ የፖለቲከኞች ስም ማጥፋት፣ አካላዊ ጥቃትና እሥራት እንደሚገጥማቸው የወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዩናይትድ ስቴትስ የፕሬስ ነፃነት ላይ የሚደቀን አደጋ በሚያሳስብ ሁኔታ እየጨመረ የመሄዱን ጉዳይ መቋቋም ያስፈልጋል ብለዋል የአንቀፅ 19 ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶማስ ሁስ።

“ይህ አደጋ በዩናይትድ ስቴትስ የመናገር ነፃነት ያላት ተፅዕኖ ማሳደር ብቻ ሳይን በዓለም ዙርያም የሚያስከትለው አደጋ አለ” ሲሉም አክለዋል።

ለመናገር ነፃነት የሚሟገተው አንቀፅ 19 የተባለው ቡድን፣ ለጋጤጠኞች መብት የቆመው ኮሚቴ፣ ዓለምቀፍ የመናገር ነፃነት ልውውጥና ሌሎች ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ቡድኖች የአሜሪካ ጋዜጠኞችን አነጋገረው ያወጡት ዘገባ ነው ይህን ክስተት የዘረዘረው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG