በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቃለ ምልልስ - ከኦነግ አመራር አቶ ቶሌራ አዳባ


በ2001 ዓ.ም የኦነግ ተዋጊዎች በሞያሌ አቅራቢያ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ በስልጠና ላይ እያሉ (ፎቶ - ሮይተርስ)
በ2001 ዓ.ም የኦነግ ተዋጊዎች በሞያሌ አቅራቢያ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ በስልጠና ላይ እያሉ (ፎቶ - ሮይተርስ)

መቀመጫውን ኤርትራ ያደረገውና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ አንጃ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲያደርግ የነበረውን የትጥቅ ትግል በጊዜያዊነት ማቆሙን ዛሬ አስታወቀ። በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ሰሞኑን በተፈፀመው ግድያና ሁከት ውስጥ እጁ እንደሌለበት ተናግሯል።

መቀመጫውን ኤርትራ ያደረገውና በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ አንጃ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲያደርግ የነበረውን የትጥቅ ትግል በጊዜያዊነት ማቆሙን ዛሬ አስታወቀ።

የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ ዳባ ስለ ውሳኔው ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፤ ድርጅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋራ የተጀመረውን የሰላም ውይይት ለማሳካት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ማወጁን አረጋግጠዋል።

አያይዘው “የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ የሚፈታ ከሆነ የግዴታ የትጥቅ ትግል ካላካሄድን አንልም” ብለዋል።

በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ሰሞኑን በተፈፀመው ግድያና ሁከት ውስጥ እጁ እንደሌለበት ተናግሯል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ቃለ ምልልስ - ከኦነግ አመራር አቶ ቶሌራ አዳባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG