በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነቀምቱ የተቃውሞ ሰልፍ መንስዔና የደምቢዶሎው ግጭት


ደምቢዶሎ
ደምቢዶሎ

“የኮማንድ ፖስት ያዘዘው ነው፣ አስተዳደሩ ሥራ ላይ ያዋለው። ከዓዋጁ ጋር አይሄድም። በመሆኑም ለሌላ ጊዜ ሁኔታዎችን አመቻችተን እንቀበላቸዋለን፤ ለአሁኑ ይመለሱ ነው የተባለው።” - አቶ ሞገስ ኤዴኤ የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ

ዛሬም በነቀምት ውጥረቱ አልረገበም። ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ በቅርቡ ከእሥር የተፈቱትን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ መሪዎች አቶ በቀለ ገርባን፣ ዶ/ር መረራ ጉዲንና ሌሎችን ለመቀበል ቁጥሩ በብዙ ሺሕ የተገመተ ሕዝብ ወደ ከተማይቱ አደባባይ ቢወጣም ወደ አካባቢው የመጣው የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ የኦፌኮ መሪዎች ከመንገድ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ዘግበናል።

ይህንኑም ተከትሎ የከተማይቱ ነዋሪ ሕዝብ በፊናው ከቅዳሜ አንስቶ በጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ መቀጠሉን ነዋሪዎች አመልክተዋል።

የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ ፖሊስ ለወሰደው እርምጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በምክኒያትነት ያቀርባል።

በሌላ ዜና የመንፈሳዊ ጉባዔ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ በነበረችው የደምቢዶሎ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት በርካቶች የቆሰሉበትንና የሰው ህይወት የጠፋበትን ድንገት ይመለከታል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የነቀምቱ የተቃውሞ ሰልፍ መንስዔና የደምቢዶሎው ግጭት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG