እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ1972 ወዲህ ጨረቃ ላይ በማረፍ የመጀመሪያዋ የሆነችው የዩናይትድ ስቴትስ የጠፈር መንኮራኩር ኦዲሲየስ የቀራት የባትሪ ኃይል ከ10 እስከ 20 ሰአታት ብቻ የሚያቆያት መሆኑን በረራዋን የሚቆጣጠሩት ባለሞያዎች አስታወቁ።
መንኩራኩሯን ከጨረቃ ጠርዝ ላይ የሚያሳርፈው ሮቦት ጋር እስካሁን ግኙነታቸው ያለመቋረጡን ጨምረው አመልክተዋል።
ቴክሳስ ክፍለ ግዛት የሚገኘው ‘ኢንቱቲቭ ማሽንስ” የተባለው የጠፈር ምርምር ኩባንያ እንዳመለከተው የበረራ ተቆጣጣሪዎቹ ዛሬም የጠፈር መንኮራኩሯን ጨረቃ ላይ ካሳረፈው የሮቦት መሳሪያ ጋር ግንኙነታቸውን መቀጠላቸውን እና ማለዳ ላይ ልዩ ልዩ የሳይንስ መረጃዎችን እና ምስሎችን መላኩን ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር ምርምር አስተዳር - ናሳ የጠፈር መንኮራኩሯን ለመስራት እና የተቋሙንና የሌሎች የግል ድርጅቶችን የምርምር መሳሪያዎች ጭና ወደ ጨረቃ እንድትመጥቅ ለማድረግ ለኢንቱቲቭ ማሽንስ የ118 ሚሊየን ዶላር ወጭ ማድረጉ ታውቋል።
መድረክ / ፎረም