በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የአሜሪካ የግል መንኮራኩር ጨረቃ ላይ እንደሚያርፍ ይጠበቃል

አንድ የአሜሪካ የግል ኩባንያ ባለፈው ሳምንት ወደ ጠፈር ያስወነጨፈው መንኮራኩር፣ ዛሬ ሐሙስ ጨረቃ ላይ እንደሚያርፍ ይጠበቃል።
አንድ የአሜሪካ የግል ኩባንያ ባለፈው ሳምንት ወደ ጠፈር ያስወነጨፈው መንኮራኩር፣ ዛሬ ሐሙስ ጨረቃ ላይ እንደሚያርፍ ይጠበቃል።

አንድ የአሜሪካ የግል ኩባንያ ባለፈው ሳምንት ወደ ጠፈር ያስወነጨፈው መንኮራኩር፣ ዛሬ ሐሙስ ጨረቃ ላይ እንደሚያርፍ ይጠበቃል።

ባለፈው ሐሙስ ሌሊት ፍሎሪዳ ከሚገኘው የኬኔዲ የጠፈር ማዕከል ከ’ስፔስ ኤክስ’ ሮኬት ላይ የተወነጨፈው መንኮራኩር፣ የአሜሪካ የህዋ ምርምር አስተዳደር (ናሳ) ለሚያካሂደው የጨረቃ ፕሮግራም፣ ከግል ኩባንያዎች ጋር በመተባበር ከሚፈጽማቸው ተልዕኮዎች አንዱ ነው ተብሏል።

አሜሪካ እንደገና ወደ ጨረቃ ሰዎችን ከመላኳ በፊት፣ ናሳ የሚያካሂደው የቅድመ ሙከራና ምርምር አካል መሆኑም ተነግሯል።

የአፖሎ ፕሮግራም ከአምሳ ዓመታት በፊት ካከተመ በኋላ፣ አሜሪካ ወደ ጨረቃ ሰውን ልካ አታውቅም።

እስከ አሁን አሜሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ እና ጃፓን መንኮራኩራቸውን በተሳካ ሁኔታ ጨረቃ ላይ ያሳረፉ ሲሆን፣ በግል ኩባንያ የተደረገ ተልዕኮ ግን እስከ አሁን ጨረቃ ላይ አላረፈም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG