አዲስ አበባ —
ቁጥራቸው በ3 ሚሊዮን ለጨመረው ለኢትዮጵያ የድርቅ ተጎጂዎች፣ የሚፈለገው ዕርዳታ አጣዳፊ መሆኑንና አሁኑኑ መመጣት እንዳለበት የተበባሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ/ቤቱ ይሄን ያስታወቀው በቅርቡ ይፋ የተደረገውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ጥያቄ ሰነድ መነሻ በማደርግ ነው፡፡
በቅርቡ ይፋ የተደረገው የሰብዓዊ ዕርዳታ ጥያቄ ሰነድ /ኤችአር ዲ/ እንዳመለከተው በድርቁ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ