በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባራክ ኦባማ የቦልትሞር መስጊድን የጎበኙት ፕሬዚደንት ከሆኑ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ተገኝተው፣ የቦልትሞር የሙስሊም ማኅበረሰብ በተባለ ተቋም የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ አሜሪካውያን ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ተገኝተው፣ የቦልትሞር የሙስሊም ማኅበረሰብ በተባለ ተቋም የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ አሜሪካውያን ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል

የፕሬዚደንቱ ጉብኝት የሚፈለግና አስደሳች እንደሆነም አንድ የእምነቱ ተከታይ ሙስሊም-አሜሪካዊ አስተያየታቸውን ለቪኦኤ ሰጥተዋል።

በአንድ ሃይማኖት ላይ የሚፈጸም ጥቃት በሁሉም እምነቶች ላይ እንደተፈጸመ ጥቃት ይቆጠራል ሲሉ፣ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ተናገሩ። የቪኦኤው ክሪስ ሲምኪንስ እንደዘገበው፣ ፕሬዚደንት ኦባማ ይህን የተናገሩት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ክፍለ-አገር ቦልቲሞር ውስጥ የሚገኝ አንድ መስጊድ ፕሬዚደንት ከሆኑ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ በጎበኙበት ወቅት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፕሬዚደንቱ ጉብኝት የሚፈለግና አስደሳች እንደሆነም አንድ የእምነቱ ተከታይ ሙስሊም-አሜሪካዊ አስተያየታቸውን ለቪኦኤ ሰጥተዋል።

ምንም እንኳ ጉብኝቱ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የመጀመርያ ቢሆንም፣ ፕሬዚደንት ኦባማ በሃይማኖት ነፃነትና እኩልነት ላይ አዎንታዊ ንግግር ሲያደርጉ የመጀመርያቸው እንዳልሆነ ነው፣ አቶ ነጂብ መሐድ የተናገሩት።

በትናንትናው እለት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባልቲሞር ከተማ የሚገኝ መስጊድ ጎብኝተው ነበር።
በትናንትናው እለት ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ባልቲሞር ከተማ የሚገኝ መስጊድ ጎብኝተው ነበር።

ፕሬዚደንት ኦባማ አጭርና ግልጥ መልዕክት ነው ያስተላለፉት።

በንንግራቸውም፣ "አንድ አሜሪካውያን ቤተሰብ ነን። የቤተሰባችን አንደኛው አካል ሲገለል ወይም እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲታይና ዒላማ ሲሆን፣ መላ አገራችን የተነካ ያህል ያማል" ሲሉ ፕሬዚደንት ኦባማ፣ በቦልቲሞሩ የእስላማዊ ማኅበረሰብ ስብሰባ ላይ የተናገሩት።

ይህንንም ያሉት፣ ከፓሪሱና ከበርናርዲኖ-ካሊፎርኒያው የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ በሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረው ጥላቻ ስላሳሰባቸው መሆኑ ተገልጧል። ይህ ፕሬዚደንቱ የጎበኙት መስጊድም፣ የጥላቻና የዛቻ ዒላማ ሆኗል ተብሏል።

"ሰዎች ብዙውን ጊዜ አሰቃቂውን የሽብርተኞች ተግባር ከመላው ሃይማኖቶች ጋር ሲያጋጩ ይታያሉ። እናም ደግሞ፣ እርግጥ ነው በቅርቡ በሙስሊም አሜሪካውያን ላይ የተነጣጠረና ይቅርታ የሌለው አጋገር ሰምተናል።" ብለዋል።

በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንታዊ ውድድር፣ ከሬፓብሊካኖቹ መካከል ቀዳሚውን ስፍር የያዙት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሙስሊሞች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ ጊዜያዊ እገዳ እንዲጣል ያቀነቀነ ሃሳብ ማሰማታቸው ይታወቃል።

አንድ አሜሪካውያን ቤተሰብ ነን። የቤተሰባችን አንደኛው አካል ሲገለል ወይም እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲታይና ዒላማ ሲሆን፣ መላ አገራችን የተነካ ያህል ያማል።
የዩናትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ

ሌሎቹ ሬፓብሊካን ተወዳዳሪዎች ግን ትራምፕ ሃሳቡን ውድቅ አድርገውታል። ፓኪስታን አሜሪካዊው አህመድ ራና እና ባለቤታቸው፣ "ምስጋና ይሁን ለፕሬዚደንት ኦባማና እንደ ሂለሪ ክሊንተን ለመሳሰሉ ዴሞክራቲክ ተወዳዳሪዎች፣ በሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረውን የጥላቻና የመገለል ዘመቻ ይቃወማሉ" ብለዋል።

አክለውም፣ "ለኦባማ፣ ድምጻችንን ሰጥተን መርጠናቸዋል። በድጋሚም ተመርጠዋል። በተለይ ሂለሪ ክሊንተን የሚያሳዩን፣ ሁላችንም ሙስሊሞች ነን የሚለው አነጋገር፣ የድጋፍ ምልክት ነው። ለሙስሊሞች ያላቸውን አክብሮትም ይገልጣል። ብዙ ሙስሊም-አሜሪካውያን የሚደግፏቸውም ይመስለኛል" በማለት ገልጸዋል።

አዲሱ አበበ ያጠናቀረው ዘገባ አለ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

ባራክ ኦባማ የቦልትሞር መስጊድን የጎበኙት ፕሬዚደንት ከሆኑ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

በጉብኝቱ ወቅት የተነሱ ፎቶዎችንም ከዚህ በታች ይመልከቱ።

በተጨማሪም፣ የንግግራቸው ቪድዮም አለ።

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ያደረጉት ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:38 0:00

XS
SM
MD
LG