የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ምክር ቤት ልጆቻችንን ከጥቃት ለመጠበቅ የቻለውን ነገር ቢያደርግስ? በማለት “በሀገራችን በጠበንጃ የሚፈጸም ሁከት ወረርሺኝ ለመቆጣጠር ዳር ያላደርስነው ስራ” ባሉት ያላቸውን ብስጭት በሳምንታዊ ንግግራቸው ላይ ገለጹ።
ባራክ ኦባማ ሁሉን የሁከት ተግባር ልናቆም አንችልም፣ ግን አንድ እንኩዋን ለማስቆም ብንሞክርስ ምን አለ? በማለት የሀገሪቱ ምክር ቤት ምንም ዓይነት ርምጃ ለመውሰድ ወረርሺኙን ለመቀነስ በተደጋጋሚ ሳይችል መቅረቱን አመልክትዋል።
ከሶስት ዓመታት በፊት በሁለቱም ፓርቲዎች ትብብር የቀረበው “Commonsense Bill” የተባለው ህግ መሳሪያ የሚገዛ ማናቸውም ሰው የግል ታሪኩ እንዲመረመር የሚያደርግ እና ሰማኒያ ከመቶው ኣሜሪካዊ የሚደግፈው እንደነበር አውስተዋል።
የብሔራዊ የ ጠመንጃ ባለቤትነት ማህበር (National Rifle Association) አብዛኞቹ አባላት የሚደግፉት እንደነበርና ያስታወሱት ፕሬዚደንቱ ሆኖም መሳሪያ ሻጭ ሎቢዪስቶች የተቃውሞ ዘመቻ እንዳካሄዱበትና የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ህጉን እንዳያልፍ እንዳከላከልው አስረድተዋል።
ባለስልጣኖቻቸው በመሳሪያ የሚፈጸም ሁከት ተግባር እንዲቀነስ የሚያስችል ኣዲስ ርምጃ እንዲያጠኑ አዝዣለሁ ያሉት ፕሬዚደንቱ የፊታችን ሰኞ ከጠቅላይ አቃቤ ህጋቸው ሎሬታ ሊንች ጋር እንደሚወያዩበት አስታውቀዋል።