በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ያቀዱት ጉዞ ላይ ምሁራዊ ግምገማ


የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአይሲል ላይ የነደፉትን ስትራተጂ ያሳወቁበትን ንግግር ሲያደርጉ - ረቡዕ፤ ጳጉሜ 5/2006 ዓ.ም - ዋይት ሃውስ ዋሺንግተን ዲሲ
የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአይሲል ላይ የነደፉትን ስትራተጂ ያሳወቁበትን ንግግር ሲያደርጉ - ረቡዕ፤ ጳጉሜ 5/2006 ዓ.ም - ዋይት ሃውስ ዋሺንግተን ዲሲ

ፕሬዚደንት ኦባማ በፊታችን ሃምሌወር ፍጻሜ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ባለፈዉ አርብ ከWhite House የወጣ መግለጫ አስታዉቋል። ኦባማ በስልጣን ላይ እያሉ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የመጀመሪያዉ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ይሆናሉ።

ኦባማ በቅድሚያ ወደ አባታቸዉ አገር ኬንያ ይጉዋዙና ጋዴዎችን ከድርጅቶች፣ ከመንግስታትና ከንግድ መሪዎች የማገናኘት ዓላማ ያለዉ ዓለም አቀፋዊ የንግድ መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ይገኛሉ። ከዚያም ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ከአገሪቱ መንግስት ባለስልጣናትና ከአፍሪቃ ህብረት መሪዎች ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተግልጿል።

የፕሬዚደንቱን ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ እንዲገመግሙልን የጠየቅናቸዉ ቀድሞ በኢትዮጵያ የUnited States አምባሳደርና አሁን በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በኤሊዬት የዓለም አቀፍ ጥናት ተቋም ዉስጥ ፕሮፌሰር David Shinn ጉብኚቱ ተገቢ ነዉ ይላሉ። በUnited States እና በኢትዮጵያ መካከል ያለዉ ግንኙነት ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ መሆኑን የሚያሳይ ይመስለኛል። ግንኙነቱ ከአጼ ሚኒልክ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ የቀጠለ ሲሆን፣ በእነዚህ ጊዜያት ሁሉ አንድ የUnited States ፕሬዚደንት ስልጣን ላይ እያለ ወይንም በስራ ዘመኑ ኢትዮጵያን ጎብኚቶ አያዉቅም።

አርብ ለት ዜናዉ እንደተሰራጨ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት Human Rights Watch ፕሬዚደንት ኦባማ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ የጎደፈዉ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ከመሪዎችዋ ጋር በግልና በይፋ ዉይይት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

David Shinn ፕሬዚደንት ኦባማ በዉይይታቸዉ ዉስጥ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሂደትና የሰብአዊ መግቶች ጉዳዮች በግል ይሁን በይፋ አሁን አይታወቅ እንጂ ሳያነሱ እንደማይቀሩ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ለትዝታ በላቸዉ ከስጡት ግምገማ ያድምጡ።

ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ያቀዱት ጉዞ ላይ ምሁራዊ ግምገማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG