በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ዮርኩ የከተማ ባቡር ጥቃት የተያዘው ሰው በሽብር ወንጀል ክስ ፍ/ቤት ይቀርባል


በኒው ዮርክ ብሩክሊን ሰፈር በሚገኘው የከተማ ማመላለሻ ባቡር ጣቢያ ተኩስ ከፍቶ አስር ሰዎች በማቁሰል የተወነጀለው የስድሳ ሁለት ዓመቱ ፍራንክ ጄምስ በሽብር ወንጀል ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል
በኒው ዮርክ ብሩክሊን ሰፈር በሚገኘው የከተማ ማመላለሻ ባቡር ጣቢያ ተኩስ ከፍቶ አስር ሰዎች በማቁሰል የተወነጀለው የስድሳ ሁለት ዓመቱ ፍራንክ ጄምስ በሽብር ወንጀል ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል

በኒው ዮርክ ብሩክሊን ሰፈር በሚገኘው የከተማ ማመላለሻ ባቡር ጣቢያ ተኩስ ከፍቶ አስር ሰዎች በማቁሰል የተወነጀለው ሰው በሽብር ወንጀል ክስ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባል።

ፍራንክ ጄምስን ትናንት ፖሊሶች በስልክ በደረሳቸው ጥቆማ ቀኑን ሙሉ ሲፈልጉት ቆይተው ማንሃተን መንገድ ላይ አግኝተው ይዘውታል።

በአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ መሰረት ለፖሊሶች ስልክ የደወለው ራሱ መሆኑን ህግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።

የስድሳ ሁለት ዓመቱ ፍራንክ ጄምስ ለከተማ ባቡር ጣቢያው ውስጥ ጢስ ከለቀቀበት በኋላ ሰላሳ ሦስት ጥይቶች በመተኮስ ክስ እንደሚመሰረትበት በኒው ዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል አቃቤ ህግ ብሬዮን ፒስ አስታውቀዋል።

"ፍራንክ ጄምስ ህጋዊ ሥልጣንም ሆነ ፈቃድ ሳይኖረው ኒው ዮርክ ብሩክሊን ሰንሴት ፓርክ በሚገኘው የከተማ ባቡር ጣቢያ ተጓዦችንና የባቡር ጣቢያውን ሰራተኞች ለመግደልና ለማቁሰል ሆን ብሎ ጥቃት ፈጽሙዋል። ከሌላ ስቴት መጥቶ ጥቃቱን ማድረሱ እና ለጥቃቱ የሚስፈልገውን መሳሪያ ይዞ መምጣቱን የሚያሳይ ምንም የማያጠራጥር ማስረጃ ልናቀርብ ተዘጋጅተናል።" ብለዋል

ፍርድ ቤት ወንጀሉን ፈጽሟል ብሎ ከፈረደበት የዕድሜ ልክ እስራት ቅጣት ሊበየንበት እንደሚችል ነው አቃቤ ህጉ የገለጹት። ግለሰቡ ከሃገር በቀልም ይሁን ከዓለም አቀፍ ሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ እንደሌለ ሆኖም ጥቃቱን በምን ምክንያት እንዳደረሰ እስከአሁን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አስታወቀዋል።

XS
SM
MD
LG