በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ጉዳይ ፈርመውት የነበረውን ትዕዛዝ አራዘሙ


ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት፣ ዋሽንግተን ዲሲ
ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት፣ ዋሽንግተን ዲሲ

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አልተሻሻለም በሚል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ከሁለት ዓመታት በፊት ፈርመው ያወጡትን ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ በአንድ ዓመት አራዘሙት።

በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ጦርነት ለአሜሪካ የውጪ ፖሊሲ እና ብሄራዊ የጸጥታ ልዩ ስጋት ነው፣ በሚል ጆ ባይደን ከሁለት ዓመት በፊት መስከረም 2014 ዓ/ም ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ አውጥተው ነበር።

ትዕዛዙ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የመብት ጥሰት በፈጸሙ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ የሚመለከታቸው የአሜሪካ ተቋማት ማዕቀብ እንዲጥሉ የሚያስችል ነበር።

“በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ፣ ብሎም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ ደህንነት እና መረጋጋት ላይ አደጋ የደቀነና እንዲሁም በአሜሪካ ብሔራዊ ጸጥታ እና የውጪ ፖሊሲ ላይ ያልተለመደ እና ልዩ አደጋ የደቀነ በመሆኑ ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዙ ለአንድ ዓመት ተራዝሟል” ሲል ትናንት በፕሬዚደነቱ ስም ከዋይት ሃውስ የወጣው መግለጫ አመልክቷል። ትዕዛዙ በፌዴራል መዝገብ ላይ ታትሞ ለአሜሪካ ም/ቤት እንደሚላክም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG