ዋሽንግተን ዲሲ —
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ግጭት “እንዲራዘም ሰበብ በሚሆኑ ተጠያቂዎችና ተባባሪዎቻቸው ላይ አዲስ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል” ያሉትን ትዕዛዝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ፈርመዋል።
ትዕዛዙ “የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን እንዲሁም ህወሃትንና የአማራ ክልላዊ መንግሥታትን በተጠያቂነት መያዝ እንዲችል” ለዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አስፈላጊ ያሉትን ሥልጣን የሚሰጠው እንደሆነ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ባይደን ትዕዛዙን ይፋ ካደረጉ በኋላ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባወጡት ለፕሬዚዳንት ባይደን ይድረስ ባሉት ባለ ሦስት ገፅ “ግልፅ ደብዳቤ” የዩናይትድ ስቴትስ ተከታታይ አስተዳደሮች በኢትዮጵያ ላይ “ይዘዋቸዋል” ባሉት “የተዛባ አመለካከት” ቅሬታ አዘል መልዕክት አስተላልፈው “ኢትዮጵያ ከሚሊዮኖች ደኅንነት ይልቅ ሥልጣንን መጠቅለልን በሚመርጡ የተከፉ ሰዎች የተቀነባበረ ተፅዕኖ ለሚያስከትላቸው መዘዞች አትንበረከክም” ብለዋል።
ከኤርትራ መንግሥትና ከህወሓት እስካሁን የተሰማ ምላሽ የለም እየተከታተልን ነን፤ የምናገኘውን እናደርሳችኋለን።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡)