በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ለዩክሬን አባልነት በራችን ክፍት ነው” የኔቶ ዋና ጸሐፊ


የኔቶ ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ
የኔቶ ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ

ኔቶ፣ ዩክሬንን በአባልነት ለመቀበል በሯ ክፍት እንደኾነና ሩሲያ የኅብረቱን መስፋፋት የመሻር ሥልጣን እንደሌላት፣ ዋና ጸሐፊው ዬንስ ስቶልትንበርግ ተናገሩ፡፡

ስቶልትንበርግ፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ኖርዌይ ኦስሎ ላይ በሰጡት ቃል፣ “ባለፉት ወራት፣ የኔቶ አባል ሀገራት እና አጋሮቻችን፣ ዩክሬናውያን ግዛታቸውን እንዲያስመልሱ ታይቶ የማይታወቅ ድጋፍ ሰጥተዋል፤” ብለዋል፡፡

“ዩክሬን አባል ለመኾን ያላትን ፍላጎት በሚመለከት ተነጋግረንበታል፡፡ በሩ፣ ለዐዲስ አባላት ክፍት እንዲኾን፣ ዩክሬንም በአባልነት እንድትገባ በሙሉ ተስማምተዋል፤” ብለዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው አያይዘውም፣ “ዩክሬን፣ መቼ አባል እንደምትኾን መወሰን ፣ የኔቶ አባላት እና የዩክሬን ፋንታ ነው፡፡ ሩስያ፣ የኔቶን የመስፋፋት ውሳኔ የመገደብ ሥልጣን የላትም፤” ብለዋል፡፡

ኪየቭ ላይ ስለደረሰው የሚሳይል ጥቃት የተጠየቁት ስቶልትንበርግ፣ በዩክሬን ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት፣ “ የጦር ወንጀል ነው፤” ብለዋል፡፡

ጥቃቱን፥ እ.አ.አ ሐምሌ 22 ቀን 2011፣ ኖሮዌይ ውስጥ 77 ሰዎች ከተገደሉበት፣ የቀኝ አክራሪዎች የሽብር ጥቃት ጋራ አመሳስለውታል፡፡

ቱርክ እና ሌሎቹም የኔቶ አባል አገሮች በሙሉ፣ ስዊድንም አባል እንደትኾን እንደጋበዙ፣ በድጋሚ የተናገሩት ስቶልተንበርግ፣ ኔቶ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ፣ “በተቻለው ፍጥነት እየሠራ ነው፤” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG