በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔቶ ዋና ጸሐፊ በዩክሬን ጉብኝት ላይ ናቸው


የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(NATO) ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ፣ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(NATO) ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ፣ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት(NATO) ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ፣ ዛሬ በዩክሬን፣ ድንገተኛ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከከፈተች ከአንድ ዓመት በኋላ፣ የኔቶው ዋና ጸሐፊ ዩክሬንን ሲጎበኙ፣ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ዋና ጸሐፊው በዋና ከተማዋ ኪየቭ የሚገኘውን በውጊያ ላይ የተገደሉ ወታደሮች መታሰቢያ ሐውልት ጎብኝተዋል፤ በጉዳት የተሰናከሉ የሩሲያ ወታደራዊ መሣሪያዎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ ስቶልትንበርግ፣ የዩክሬን ኃይሎችን በመሣሪያ የሚረዱ የኔቶ አባል አገሮችን እንደሚደግፉ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ወረራ ተከትሎ፣ የኔቶ አባል ሀገራት ቁጥር ጨምሯል፡፡ ባለፈው ወር፣ ፊንላንድ ኅብረቱን ተቀላቅላለች፡፡ የፊንላንድ ጎረቤት ስዊድንም ያስገባቸው የአባልነት ማመልከቻ፣ ከሀንጋሪ እና ከቱርክ በስተቀር በአባል ሀገራቱ በሙሉ ጸድቆላታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኔቶ አባሎች፥ ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ፣ ለዩክሬን የሚኾኑ 14 ሌፐርድ 2 ኤ 4 ታንኮችን በጋራ ገዝተው ለማደስ ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ታንኮቹን፣ እአአ 2024 መባቻ ላይ፣ ለዩክሬኑ ስምሪት ዝግጁ እንደሚሆኑ፣ የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች አስታውቀዋል፡፡ ዩክሬን፥ ወታደሮቿ የሩሲያን ኃይሎች የመገዳደር ዐቅም እንዲያፈረጥሙ፣ የኔቶ አባል ሀገራት፣ ታንክ እና መሰል ከባድ መሣሪያዎችን እንዲሰጧት ጠይቃለች፡

XS
SM
MD
LG