በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታጋች ተማሪዎች ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በቤዛ ክፍያ የተለቀቁ ተማሪዎች ገለጹ


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ
የታጋች ተማሪዎች ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በቤዛ ክፍያ የተለቀቁ ተማሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:35 0:00

ከሁለት ሳምንት በፊት፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ እስከ አሁን በታጣቂዎች ታግተው የሚገኙ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው፣ በቅርቡ “የቤዛ ገንዘብ ከፍለን ተለቀናል” ያሉ ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸውን በምስጢር እንድንይዝ የጠየቁን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት ተማሪዎች፣ “ሸኔ” ብለው በጠሩት ታጣቂ ቡድን ታግተው መቆየታቸውንና ከ50 ሺሕ እስከ 300ሺሕ ብር የቤዛ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በታጣቂ ቡድኑ ቁጥጥር ሥር በነበሩባቸው ቀናት፣ “ብዙ ድብደባ እና እንግልት ይደርስብን ነበር፤” ያሉት ተማሪዎቹ፣ አሁንም በታጣቂዎቹ እጅ እንደሚገኙ የጠቆሟቸው 67 ታጋቾች፣ “በከፍተኛ ሥቃይ ውስጥ መኾናቸው በእጅጉ አሳስቦናል፤” ሲሉም አመልክተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG