በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከታገቱት ተማሪዎች የሚበዙት አስለቅቀናል” የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት


ፎቶ፦ አቶ ኃይሉ አዱኛ
ፎቶ፦ አቶ ኃይሉ አዱኛ

“አልተለቀቁም” የታጋቾች ቤተሰቦች

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ፣ በገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ ከታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥቂቶች ሲቀሩ የሚበዙትን አስለቅቀናል ቢልም፣ ቤተሰቦቻቸው ግን እንዳልተለቀቁና የተለቀቁም ካሉ እንዳላገኟቸው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ "ሸኔ" ሲሉ በጠሯቸው ታጣቂዎች እንደታገቱ ከገለጿቸው 167 ተማሪዎች ውስጥ፣ “እስከ ትላንት ምሽት ድረስ፣ 160ዎቹን በማስለቀቅ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ችለናል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

“ከታገቱት ተማሪዎች የሚበዙት አስለቅቀናል” የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:51 0:00

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የታጋች ተማሪዎች ቤተሰቦች ግን፣ የነሱ ቤተሰብ የሆኑ ታጋቾች እንዳልተለቀቁ እና አሁንም እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር ማስለቀቂያ እየተጠየቁ መኾናቸውን አመልክተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለተማሪዎቹ እገታ ተጠያቂ ያደረገው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ውንጀላውን አስተባብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG