በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካና ቻይና በኮሪያ ጉዳይ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

ዩናይትድ ስቴትስ ከፊሊፒንስ፣ ከታይላንድ እና ከማሌዥያ ጋር ባሏት የኢኮኖሚና የፀጥታ ትብብር ጉዳዮች ላይ ለመምከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሬክስ ቲለርሰን ወደዚያው ተጉዘዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ከፊሊፒንስ፣ ከታይላንድ እና ከማሌዥያ ጋር ባሏት የኢኮኖሚና የፀጥታ ትብብር ጉዳዮች ላይ ለመምከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሬክስ ቲለርሰን ወደዚያው ተጉዘዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአሁኑ ጉዞ ዋና አጀንዳ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ጦር መሣሪያ መርኃግብር ከዋና ዋናዎቹ የመነጋገሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።

ሚስተር ቲለርሰንና የደቡብ ኮሪያ አቻቸው ፊሊፒንስ ዋና ከተማ ማኒላ ላይ በተቀመጠው የደቡብ ምሥራቅ እሥያ ሃገሮች ማኅበር ስብሰባ ላይ ትናንት አብረው ተገኝተዋል።

ይህ የሃገሮቹ የማኒላ ጉባዔ የተካሄደው ሰሜን ኮሪያ በምታስወነጭፋቸው ተምዘግዛጊ ማሣይሎችና ሙከራዎቿ ሳቢያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በክብደቱ ከዚህ ቀደም ያልተስተዋለ ማዕቀብ በጣለባት በማግሥቱ ነው።

አሜሪካና ቻይና በኮሪያ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:53 0:00

የመንግሥታቱ ድርጅት በሰሜን ኮሪያ የከሰል፣ የብረት፣ የእርሣስና የአሣ ወጭ ንግዶች ላይ ያሳረፈው ብርቱ ዱላ የፒዮንግያንግን የምጣኔኃብት አከርካሪ የሚፈታተን እንደሆነ ተነግራል።

ያንን በፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ያለፈ ማዕቀብ ቻይናም በመደገፏ ዩናይትድ ስቴትስ አድናቆቷን ገልፃለች።

ቻይና በኮምዩኒስት ጎረቤቷ ላይ የሚወሰዱ የቅጣት እርምጃዎችን ስትቃወም ወይም ላለመቀበል ስታገራግር ብትቆይም ትናንት ማኒላ ላይ የፈረመችው ሰነድ ግን የሃሣብ ለውጥ እያሳየች እንደሆነ የሚጠቁም ፍንጭ ነው ተብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አሜሪካና ቻይና በኮሪያ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:28 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG