በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ልጅን ያህል ነገር ያለበትን ሳላውቅ እንዴት ዝም ልበል?" የዮናታን ተስፋዬ እናት የእስረኛ ቤተሰቦችን አናግረናል


ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2016 ሲቃጠል (ፎቶ፡ ፎርቹን)
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2016 ሲቃጠል (ፎቶ፡ ፎርቹን)

ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በሌላ በኩል ቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸው የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻሉና ሊጠይቁ በሄዱበት ወቅት እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

ቅዳሜ እለት በአዲስ አበባ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን የመንግስት ኮሙዩኒኬኘን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል ።

በሌላ በኩል ቂልንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ታሳሪ ቤተሰቦቻቸው የት እንደሚገኙ ማወቅ እንዳልቻሉና ሊጠይቁ በሄዱበት ወቅት እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞው የሰማያዊው ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ እናት ወ/ሮ ሙጪት ተካ ልጃቸው ያለበትን ባለማወቃቸው ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ወ/ት ቦንቱ በቀለ፣ የአቶ ደጀኔ ጣፋ ባለቤት ወ/ሮ አሰለፈች ሙላትና የመኢአድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አሰጋ አሰፋ ልጅ ወ/ት ህይወት አሰፋ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ሁኔታ አለማወቃቸው ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።

የጽዮን ግርማ ዘገባ ሙሉውን ታሪክ ይዟል።

"ልጅን ያህል ነገር ያለበትን ሳላውቅ እንዴት ዝም ልበል?" የዮናታን ተስፋዬ እናት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:56 0:00

XS
SM
MD
LG