በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ ቀሪ ምስክር የማሰማት መብቱ ታለፈ


ንግስት ይርጋ
ንግስት ይርጋ

የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በአማራ ክልል ዓመፅ አነሳስተዋል በሚል በእነ ንግሥት ይርጋ መዝገብ ክስ በመሰረተባቸው ስድስት ሰዎች ላይ፤ “ቀሪ ምስክሮቹን ለማቅረብ አንድ ዓይነት ምክንያት እየሰጠ ተደጋጋሚ ቀጠሮ በመጠየቁ ምስክሮቹን የማሰማት መብቱ ታልፏል” ሲል ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት ትዕዛዝ ሰጠ።

በተጨማሪም ንግስት ይርጋ በማረሚያ ቤት ቆይታዋ ከቤተሰብ መጠየቅ ጋር በተያያዘ ስማቸው ከተመዘገው ውጪ ቤተሰብ ሊጠይቃት እንዳልቻለ፣ ቤተሰቦቿ ከጎንደር ድረስ ተጉዘው ሊጠይቋት ሲምጡ አልተመዘገባችሁም በሚል እንደሚመለሱና ከሌሎች እስረኞች በተለየ ለ30 ደቂቃ ብቻ እንደምትጠየቅ በመግለጽ ላቀረበችው አቤቱታ የማረሚያ ቤት ሃላፊ ምላሽ እንዲሰጥበት ታዞ ለሃምሌ 20/2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠቷል።

ተከሳሾቹ የተከሰሱበት ጉዳይ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አመፅ በማስነሳት፣ አመፁን በመምራትና በማስተባበር ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር የሽብርተኝነት ድርጊት ፈፅመዋል የሚል እንደሆነና ተከሳሾቹ ክሱን መቃወማወቸው ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ዐቃቤ ሕግ ቀሪ ምስክር የማሰማት መብቱ ታለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:14 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG