በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይሻ መሐመድ ወደ መከላከያ ሚኒስቴር ተመለሱ


በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አይሻ መሐመድ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አይሻ መሐመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 12 / 2016 ዓ.ም. ለሦስት ባለሥልጣናት ሹመትና የቦታ ዝውውር ፅህፈት ቤታቸው አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው የቦታ ዝውውር እርምጃችው የመስኖና የቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር የነበሩትን አይሻ መሐመድን ወደ መከላከያ ሚኒስትርነት መልሰው ላለፉት ሁለት ዓመታት በመከላከያ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩትን ዶ/ር አብርሃም በላይን ቦታ አይሻ መሃመድ ወደለቀቁት ቦታ አዛውረዋል።

በ2011 ዓ.ም. በተመሠረተው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ካቢኔ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አይሻ መሐመድ ከተሾሙ ከወራት በኋላ ተነስተው ቀድሞ ይመሩት ወደነበረው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተመልሰው ነበር። በ2014 ዓ.ም. በተካሄደው የካቢኔ ምሥረታ አዲስ የተዋቀረውን የመስኖና የቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር እንዲመሩ ተሹመው ሲሠሩ ቆይተዋል።

የቅየሳ ባለሙያ የሆኑት አይሻ መሐመድ ወደ ፌደራል ሥልጣን ከመሻገራቸው በፊት የአፋር ክልል የአደጋ መከላከል ቢሮ ኃላፊ ነበሩ። ቀደም ሲል እዚያው አፋር ክልል ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሆነውም ሠርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱን ሚኒስትሮች ቦታ ያቀያየሩበት ምክንያት አልተገለፀም።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ በሚኒስትር ደ’ኤታ ማዕረግ ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል መዛወራቸው ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG