በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ከ30 ከብት ሁለት ብቻ ቀረኝ" - የቦረና አርብቶ አደር


ድርቁ ከብቶቻቸውን እየጨረሰ መሆኑን የቦረና አርብቶ አደሮች ተናገሩ። ከሦስት ወራት በፊት ስናነጋግራቸው ከ30 ከብት ሃያ እንደቀራቸው ነግረውን የነበሩት አርብቶ አደር አሁን ሁለት ብቻ እንደቀራቸው ነግረውናል።

በኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ክልሎች የደረሰው ድርቅ አሁንም የቦረና እና ጉጂ ዞኖች፣ የሶማሌ ክልል እና በደቡብ ክልል የኮንሶ ወረዳን እያጠቃ መሆኑንና በዚህም በዋነኛነት ከብቶቻቸው ሙሉ ለሙሉ እያለቁባቸው መሆኑን ገለፁ።

የኦሮሞያ ክልል የአደጋ ስጋት እና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር የፌደራሉና የክልል መንግስት በቅንጅት ሆነው ከፍተኛ እርዳታ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

"ከ30 ከብት ሁለት ብቻ ቀረኝ" - የቦረና አርብቶ አደር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:17 0:00

XS
SM
MD
LG