የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቤት ውስጥ እስር ነፃ እንዲለቀቁ ለፌደራል ፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ደብዳቤ መጻፉን ፓርቲው አድንቋል።
የፓርቲው ጊዜያዊ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ፤ "ምርጫ ቦርድ ለመንግሥት ፀጥታ አካል ደብዳቤ መፃፉ አንድ እርምጃ ነው” ብለውታል።
“አቶ ዳውድ ኢብሳ ለ11 ወራት የመንቀሳቀስ መብታቸው ተገድቦ በቤት ውስጥ መቆየታቸው ከሕግ አግባብ ውጭ ነው” ሲል የምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት ለመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል።