በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አብን የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ክልሉ “ሕጋዊ አይደለም” ብሎታል


አብን
አብን

በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በሚኖሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት መንግሥት እንዲያስቆም ያሚጠይቅ ሰልፍ ለማካሄድ ጥሪ ማድረጉን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለፀ።

“በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም በተደጋጋሚ ለፌደራልና ለክልል ባለሥልጣናት አስታውቀናል ሰሚ ግን አላገኘንም።” ሲሉ የንቅናቄው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ከነገ በስቲያ ዕረቡ ጥቅምት 18/2013 ዓ.ም የተጠራው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች እንደሚካሄድ አቶ ጣሂር አስታውቀዋል። የአማራ ክልል መንግሥት ግን፤ “ሰልፉ ሕጋዊ አይደለም” ሲል ማምሻውን መግለጫ ሰጥቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አብን የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ክልሉ “ሕጋዊ አይደለም” ብሎታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:08 0:00


XS
SM
MD
LG