በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመይንማር ”ብሄራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ ፓርቲ” ድል ተቀናጀ


በመይንማር (Myanmar) ተቃዋሚው ”ብሄራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ ፓርቲ” በመንግሥቱና በወታደሮች በሚደገፈው “Union Solidarity and Development” በተሰኘው ፓርቲ ላይ ድል ተቀዳጅቶ የፓርላማውን አብዛኛ መቀመጫ ማሸነፉ ይፋ ተደረገ።

የብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽኑ የመጨረሻውን የድምፅ ቆጠራ ውጤት በኦፊሴል ያስታወቀው በዛሬው እለት ነው።

የመይንማር (Myanmar) ጦር ሠራዊትና ትላልቆቹ የሃገሪቱ ፓርቲዎች ለፕሬዘዳንትነት የሚቀርቡትን እጩዎች የሚመርጡት በመጪው የካቲት ይሆናል ተብሏል።

”ብሄራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ ፓርቲ”ን ለዚህ ከፍተኛ ድል ያበቁት መሪ አውንግ ሳን ሱ (Aung San Suu Kyi) ግን ወታደራዊው መንግሥት ሕገ መንግሥቱ ውስጥ እንዲታከል ባደረገው ማሻሻያ አንቀጽ ምክንያት በእጩነት መቅረብ አይችሉም። የዜና ዝርዝሩን ያዳምጡ።

የመይንማር ”ብሄራዊ ሊግ ለዲሞክራሲ ፓርቲ” ድል ተቀናጀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:45 0:00

XS
SM
MD
LG