በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

​ሙሉቀን መለሰ አረፈ


​ሙሉቀን መለሰ አረፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:06 0:00

​ሙሉቀን መለሰ አረፈ

ሙሉቀን መለሰ ባደረበት ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በ69 ዓመት ዕድሜው ትላንት ማረፉን አንድ የቤተሰቡ አባል ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

ሙሉቀን መለሰ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ ላለፉት አርባ ዓመታት በዩናይትድ ስቴትስ በቪርጂንያ ግዛት ውስጥ ኖሯል።

በ1946 ዓ.ም. በጎጃም ጠቅላይ ግዛት አነደድ ወረዳ ልዩ ስሙ ዳማ ኪዳነ ምሕረት በሚባል መንደር የተወለደው ሙሉቀን በስድስት ዓመቱ ከአጎቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መምጣቱን የህይወት ታሪኩን የሚዘክር ጽሑፍ ይጠቁማል።

የ12 ዓመት አዳጊ ሆኖ በምሽት ክለቦችና በሙዚቃ ቡድኖች ውስጥ መዝፈን የጀመረው ሙሉቀን ከሁለት ዓመት የምሽት ክለቦች ቆይታ በኋላ በ1960 ዓ.ም. የፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራን ተቀላቅሏል።

​ሙሉቀን መለሰ
​ሙሉቀን መለሰ

“እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በተሰኘችው መድረክ ላይ ባዜማት የመጀመሪያ ዘፈኑ የመጀመሪያ አድናቂዎቹን አገኘ።

ሌላዋ ከፍተኛ ዝና የተጎናፀፈባት ዘፈኑ “ሄደች አሉ” በ1964 ዓ.ም. በሸክላ ተቀርፃ ስትወጣ፣ ከሦስት ዓመታት በኋላ “ወተቴ ማሬ” እና “እቴ እንዴት ነሽ ገዳዎ” የተሰኙት ዜማዎቹ በተመሳሳይ በሸክላ ታትመው አድማጭ ጆሮ ደረሱ። ሙሉቀን ለየት ያለ አጨዋወቱ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። ሙሉቀን መለሰ ባሕላዊ እና ዘመናዊ ስልቶችን አዋኅዶ በመጫወትም ይታወቃል።

ሙሉቀን ከታወቀባቸው በርካታ ዘፈኖች መካከል ‘ምነው ከረፈደ፣’ ‘ይረገም ይህ ልቤ፣’ ‘ሌቦ ነይ፣’ ‘ወድጀሽ ነበረ፣’ ‘ናኑናኑ ነይ’ ‘ላኪልኝ፣’ ‘ተነሽ ከልቤ ላይ፣’ ‘ውሃ ዋላዋይ፣’ የሚሉት ይገኙበታል።

በ1980 ዓ.ም. ወደ አሜሪካ ከገባ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ አያውቅም። በዚያው ነው ወደ መንፈሳዊ መዝሙር እንደገባ የቀረው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG