በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞቅዲሾን ከባድ የቦንብ ፍንዳታ የአልሸባብ የቀድሞ መሪ አወገዘ


ፎቶ ፋይል፡- ሙክታር ሮቦው
ፎቶ ፋይል፡- ሙክታር ሮቦው

ቅዳሜ ዕለት ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ ቢያንስ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰው የተገደለበትን ከባድ የቦምብ ፍንዳታ የጽንፈኛ ቡድን የአልሸባብ የቀድሞ ከፍተኛ መሪ አወገዘ።

ቅዳሜ ዕለት ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ ቢያንስ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰው የተገደለበትን ከባድ የቦምብ ፍንዳታ የጽንፈኛ ቡድን የአልሸባብ የቀድሞ ከፍተኛ መሪ አወገዘ።

የቀድሞ የአልሸባብ ምክትል ኤሚር የነበረው ሙክታር ሮቦው ዛሬ ሰኞ ለቁስለኞች ደም ለመለገስ በተገኘበት በሞቅዲሾ መዲና ሆስፒታል በሰጠው ቃል ጥቃቱን

“እጅግ አሳዛኝ አረመኒያዊ ተግባር” ሲል ገልጾታል።

“ይህን ተግባር የፈፀሙ፣ እጃቸው ያለበት ሁሉ የሙስሊሞችን ደም ማፍሰስ ማቆምና ንስሃ መግባት አለባቸው፣ ንፁሃንን ገድለው ገነት አይገቡም” ብሉዋል።

ለዚህ በሶማሊያ ታሪክ በአንድ ቦምብ ጥቃት በተገደሉ ሰዎች ብዛት ከምንጊዜውም የከፋ ለሆነው ፍንዳታ ኃላፊነት የወሰደ ወገን የለም። የሶማሊያ መንግሥትና የሽብርተኝነት ጉዳይ ኤክስፐርቶች ግን የአልሸባብ ሥራ እንደሆነ አጥብቀው ያምናሉ።

የሶማሊያ መንግት የሦስት ቀን ብሔራዊ ሃዘን እንዲደረግ እና የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አውጁዋል። የሶማሊያ ፕሬዚደንት አብዱላሂ ፋርማጆ ጥቃትን አረመኔያዊ ሲሉ አውግዘዋል።

በዋሽንግተን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥቃቱን እጅግ በጣም ኣውግዟል።

በዚህ ትርጉም የለሽ እና የፈሪ ጥቃት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ከሶማሊያ መንግሥት፣ ህዝብና ዓለምቀፍ ኣጋሮች ጋር መቆሟን ትቀጥላለች፣ ሽብርተኝነትን መዋጋቷን እና ሰለም፣ ፀጥታና ብልፅግና እንዲሰፍን የሚያደርጉትን ጥረት መደገፏን ትቀጥላለች ብሉዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG