ዋሽንግተን ዲሲ —
በዚሁ ጥቃት፣ እዚያ የሚገኘውን የቪኦኤ ጋዜተኛ ጨምሮ፣ ከ300 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።
የሶማልያው ፕሬዚደንት ሞሓመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በሰጡት መግለጫ፣ ለሰለባዎቹ የሦስት ቀን ብሔራዊ ሐዘን እንደሚደረግና የሀገሪቱም ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ አስታውቀዋል።
ፕሬዚደንቱ አክለው እንደተናገሩት ፤ «በሽብርተኛነት ላይ መተባበሪያና በጋራ መጸለያ ጊዜው አሁን ነው፣ ሽብር አሸናፊ አይሆንም» ብለዋል።
በጭነት ተሽከርካሪ ላይ የተጠመደው ቦምብ ትናንት ማለዳ ላይ የፈነዳው፣ ሞቅዲሾ ውስጥ የትራፊክ መጨናነቅ በሚበዛበት ዞቢ አካባቢ በሚገኘው መጋጠሚያ መንገድ ላይ መሆኑ አይዘነጋም።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ