በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የአስቸኩዋይ ምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ቁጥር ይጨምራል ተባለ


በበልግ ዝናብ መቅረትና ኤልኚኞ ባስከተለዉ ድርቅ ምክንያት የአስቸኩዋይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር 8.2 ሚሊዮን መድረሱ ይታወቃል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ድርጅት ኦቻ (UNOCHA)ጭምር የተረጂዎች ቁጥር 15 ሚሊዮን ይደርሳል እያሉ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግስት ግን የመሔሩን ግምገማ መነሻ ያደረገ አዲስ የተረጂዎች ቁጥር የፊታችን ታህሣሥ ወር ይፋ እንደሚደረግ እየገለጸ ነዉ።

ለድርቁ አደጋ ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመዉ ብሔራዊ ኮሚቴ ጸሐፊ፣ አቶ ምትኩ ካሳ ሰሞኑን ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቁጥሩ እንደሚጨምር ጠቆም አድርገዋል። በትክክል የሚታወቀዉ ግን ሰነዱ ይፋ ሲደረግ እንደሆነ አስረድተዋል።

እስክንድር ፍሬዉ ከአቶ ምትኩ ካሣ ጋር የደረገዉን ቃለ ምልልስ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

በኢትዮጵያ የአስቸኩዋይ ምግብ እርዳታ የሚፈልጉ ቁጥር ይጨምራል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:33 0:00

XS
SM
MD
LG