ድሬዳዋ —
በአፋር ክልል ገዳማይቱ በተባለች ወረዳ በመስክ ሥራ ላይ የነበሩ ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታወቀ። በሌላ በኩል እነዚህ ሁለት የመስሪያ ቤቱ ባልደረቦች ከመገደላቸው አስቀድሞ ሰኞ ዕለት በርካታ የኢሳ ሶማሌዎች በአፋር ልዩ ኃይሎች ተገድለዋል ሲል የጎሳው ኡጋዛዊ ምክር ቤት አባላትና እና የሃገር ሽማግሌዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለትም የፌዴራል መከላከያ ሰራዊት ወደገዳማይቱ ወይም ገርበኢሴ ከተማ ገብቶ እርምጃ እየወሰደ ነው ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።