በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ 1.7 ሚሊየን ሰው አደጋ ላይ ነው


በጎርፍ የተጥለቀለቁ የቤልደዴድ ከተማ ጎዳናዎች፤ ሶማሊያ
በጎርፍ የተጥለቀለቁ የቤልደዴድ ከተማ ጎዳናዎች፤ ሶማሊያ

መካከለኛ ሶማሊያ ውስጥ በደረሰው ከፍተኛ መጥለቅለቅ 1.7 ሚሊየን የሚሆኑ ሶማሊያዊያን የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረ።

በለድዌይን ከተማና በአካባቢዋ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ብዙ ሰው ያፈናቀለ ሲሆን አደጋው ቀደም ሲል ተፈናቅለው ችግር ላይ በነበሩ ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል።

ጎርፉ ከብቶችንም የወሰደ ሲሆን መሠረታዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸውና ቤቶቻቸውን ያጡ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች አፋጣኝ እርዳታ ሊደርስላቸው እንደሚገባ እየተወራ ነው።

ጎርፉ ቀድሞውንም የነበረውን “አስከፊ” ያሉትን ሁኔታ እንዳባባሰው በዓለምአቀፉ የነፍስ አድን ኮሚቴ የምሥራቅ አፍሪካ የቀውጢ ጊዜ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሻሽዋት ሳራፍ አመልክተዋል።

አንድ የሶማሊያ የአደጋ አመራር ከፍተኛ ባለሥልጣን አደጋው 53 መግደሉን ለአሶሲየትድ ፕሬስ ገልፀዋል።

ቀውሱ በመላ ሶማሊያ እንደሚስተዋልና ወደ አይሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን ጨምሮ የዋና ከተማዪቱ አውራ መንገዶች ሳይቀር መጥለቅለቃቸው ተነግሯል።

ሶማሊያ ጎረቤቶቿን ኢትዮጵያና ኬንያን ጨምሮ ከቆዩበት የተራዘመ ድርቅ ለማገገም እየታገለች ቢሆንም የምግብ ዋስትና እጦትና የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተጠቅሷል።

ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ሰሞኑን ጎርፍ ያፈናቀለው ሰው ቁጥር ከሦስት ሚሊየን መብለጡን የነፍስ አድን ኮሚቴው ሻሽዋት ሳራፍ ጠቁመው ሶማሊያ ውስጥ 1 ሚሊየን ተኩል ሄክታር ማሳ ተጥለቅልቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG