በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ በጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ መቶ ተጠጋ


በጎርፍ የተጥለቀለቁ የቤልደዴድ ከተማ ጎዳናዎች፤ ሶማሊያ
በጎርፍ የተጥለቀለቁ የቤልደዴድ ከተማ ጎዳናዎች፤ ሶማሊያ

በሶማሊያ ሰሞኑን በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ አንድ መቶ እየተጠጋ መሆኑን እና ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በጎርፉ ሳቢያ ችግር ላይ መውደቃቸውን የአገሪቱ ካቢኔ ዛሬ አስታውቋል።

ሚሊዮኖችን ለቸነፈር ካጋለጠው ድርቅ የወጣችው ሶማሊያ፣ በአፍሪካ ቀንድ እንደሚገኙ ሌሎች አገራት ሁሉ በከባድ ዝናብ እና ጎርፍ ተመታለች፡፡

ጎርፉ 700 መቶ ሺሕ ሰዎችን ሲያፈናቅል፣ መንደሮችን እና ማሳዎችን ውጦ ድልድዮችን አፍርሷል። መንግስት በያዝነው ወር የአስቸውኳይ ግዜ አዋጅ ማውጣቱ ይታወሳል።

የብሔራዊ አደጋ መከላከል መ/ቤቱን ማብራሪያ ዛሬ ሐሙስ ያደመጠው ካቢኔ፣ 96 ሰዎች እንደሞቱ እና ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በጎርፉ ምክንያት ለችግር መጋለጣቸውን አስታውቋል።

ከባድ ዝናቡ “ኤል ኒኞ” በተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እንደተከሰተ እና እስከ ሚያዚያ ወር ድረስ ሊቀትጥል እንደሚችል ታውቋል።

የአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ለውጦች እና አደጋዎች ተጋላጭ ቀጠና እንደሆነም ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG